በዚያች ሌሊት እግዚአብሔር እንደ ተጠየቀው አደረገ፤ ምድሩ በሙሉ በጤዛ ሲሸፈን፣ ባዘቶው ብቻ ደረቅ ሆነ።
“ከጥልቁ ጥልቅ ወይም ከከፍታው ከፍታ ምልክት እንዲሰጥህ ከእግዚአብሔር ከአምላክህ ለምን።”
ከዚያም ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “እባክህ አትቈጣኝ፤ አንዲት ጥያቄ እንደ ገና ልጠይቅ። በጠጕሩ ባዘቶ ላይ ሌላ ሙከራ እንዳደርግ ፍቀድልኝ፤ በዚህ ጊዜ ምድሩ ሁሉ በጤዛ ተሸፍኖ ባዘቶው ደረቅ ይሁን።”
ይሩባኣል የተባለው ጌዴዎን፣ ከርሱም ጋራ የነበሩት ሰዎች ሁሉ በጧት ተነሥተው በሐሮድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። የምድያማውያንም ሰፈር እስራኤላውያን ከሰፈሩበት በስተሰሜን በኩል፣ በሞሬ ኰረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበር።