ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “በተናገርኸው መሠረት እስራኤላውያንን በእጄ የምታድናቸው ከሆነ፣
አብራምም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህችን ምድር እንደምወርሳት በምን ዐውቃለሁ?” አለ።
ኢሳይያስም፣ “እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ እንደሚፈጽም ምልክቱ ይህ ነው፤ ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት ይቅደምን? ወይስ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ይመለስ?” ሲል ጠየቀው።
“ከጥልቁ ጥልቅ ወይም ከከፍታው ከፍታ ምልክት እንዲሰጥህ ከእግዚአብሔር ከአምላክህ ለምን።”
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ዐማኑኤል ትለዋለች።
ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደ ኢየሱስ ቀርበው ሊፈትኑት ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ጠየቁት።
በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ወደ እርሱ ዘወር ብሎ፣ “ሂድ፤ ባለህ ኀይል እስራኤላውያንን ከምድያማውያን እጅ ነጻ እንድታወጣ የምልክህ እኔ አይደለሁምን?” አለው።
እግዚአብሔርም፣ “በርግጥ እኔ ከአንተ ጋራ እሆናለሁ፤ ምድያማውያንንም እንደ አንድ ሰው አድርገህ ትመታቸዋለህ” አለው።
እነሆ፤ የበግ ጠጕር ባዘቶ በዐውድማው ላይ አኖራለሁ። ምድሩ በሙሉ ደረቅ ሆኖ ባዘቶው ላይ ብቻ ጤዛ ቢኖር፣ እንዳልኸው እስራኤላውያንን በእኔ እጅ እንደምታድናቸው ዐውቃለሁ።”
ነገር ግን፣ ‘ወደ እኛ ውጡ’ ካሉን፣ እግዚአብሔር እነርሱን በእጃችን አሳልፎ የሰጠን ለመሆኑ ምልክቱ ይህ ስለ ሆነ፣ ወደ እነርሱ እንወጣለን።”