ተራሮች በሲና አምላክ በእግዚአብሔር ፊት፣ በእስራኤልም አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ተናወጡ።
እርሱ ምድርን ሲመለከት፣ ትንቀጠቀጣለች፤ ተራሮችም እርሱ ሲዳስሳቸው ይጤሳሉ።
ተራሮች እንደ አውራ በግ፣ ኰረብቶችም እንደ ጠቦት ዘለሉ።
በሲና አምላክ፣ በእግዚአብሔር ፊት፣ በእስራኤል አምላክ፣ በእግዚአብሔር ፊት፣ ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ሰማያትም ዶፍ አወረዱ።
እግዚአብሔር ሆይ፣ በቂ ዝናብ አዘነብህ፤ ክው ብሎ የደረቀውን ርስትህን አረሰረስህ።
ተራሮች በእግዚአብሔር ፊት፣ በምድርም ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ።
የሲና ተራራ እግዚአብሔር በእሳት ስለ ወረደበት በጢስ ተሸፍኖ ነበር። ጢሱ ከምድጃ እንደሚወጣ ጢስ ወደ ላይ ተትጐለጐለ፤ ተራራውም በሙሉ በኀይል ተናወጠ።
ሕዝቡም መብረቁንና ነጐድጓዱን የተራራውን መጤስና የመለከቱን ድምፅ ባዩና በሰሙ ጊዜ በፍርሀት ተንቀጠቀጡ፤ በርቀትም ቆሙ፤
እኛ እኮ ጥንትም የአንተው ነን፤ እነርሱን ግን አንተ አላገዝሃቸውም፤ በስምህም አልተጠሩም።
ተራሮች በፊቱ ታወኩ፤ ኰረብቶችም ቀለጡ። ምድር በፊቱ፣ ዓለምና በውስጧ የሚኖሩት ሁሉ ተናወጡ።
ተራሮች አዩህ፤ ተጨነቁም፤ የውሃ ሞገድ ዐልፎ ሄደ፤ ቀላዩ ደነፋ፤ ማዕበሉንም ወደ ላይ አነሣ።
ሊዳሰስ ወደሚችለውና በእሳት ወደሚቃጠለው ተራራ፣ ወደ ጨለማው፣ ወደ ጭጋጉና ወደ ዐውሎ ነፋሱ አልደረሳችሁም፤