በእግሯ ሥር ተደፋ፤ ወደቀ፤ በዚያም ተዘረረ፤ በእግሯ ሥር ተደፋ፤ ወደቀ፤ በተደፋበት በዚያ ወደቀ፤ ሞተም።
“እግዚአብሔርን መጠጊያ ያላደረገ፣ ነገር ግን በሀብቱ ብዛት የተመካ፣ በክፋቱም የበረታ፣ ያ ሰው እነሆ!”
በምትፈርዱበትም ፍርድ ይፈረድባችኋል፤ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል።
ምክንያቱም ምሕረት ያላደረገ ሁሉ ያለ ምሕረት ይፈረድበታል፤ ምሕረት በፍርድ ላይ ያይላል።
እጇ ካስማ ያዘ፤ ቀኝ እጇም የሠራተኛ መዶሻ ጨበጠ፤ ሲሣራን መታችው፤ ራሱንም ተረከከችው፤ ክፉኛ ወጋችው፤ ጆሮ ግንዱን በሳችው።
“የሲሣራ እናት በመስኮት ተመለከተች፤ በዐይነ ርግቡ ቀዳዳም ጮኻ ተጣራች፤ ‘ለምን ሠረገላው ሳይመጣ ዘገየ? የሠረገሎቹስ ድምፅ ለምን ጠፋ?’ አለች።