“የቄናዊው የሔቤር ሚስት ኢያዔል፣ ከሴቶች ሁሉ የተባረከች ትሁን፤ በድንኳን ከሚኖሩ ሴቶች ሁሉ የተባረከች ትሁን።
አብራምንም እንዲህ ሲል ባረከው፤ “ሰማይንና ምድርን የፈጠረ ልዑል አምላክ አብራምን ይባርክ፤
የሚገባትን ሽልማት ስጧት፤ ሥራዋም በየአደባባዩ ያስመስግናት።
መልአኩም እርሷ ወዳለችበት ገብቶ፣ “እጅግ የተወደድሽ ሆይ! ሰላም ለአንቺ ይሁን፤ ጌታ ከአንቺ ጋራ ነው፤ አንቺ የተባረክሽ ነሽ” አላት።
ድምፅዋን ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች፤ “አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።
በአሦር ንጉሥ በኢያቢስና በቄናዊው በሔቤር ጐሣ መካከል መልካም ግንኙነት ስለ ነበር ሲሣራ በእግሩ ሸሽቶ የቄናዊው የሔቤር ሚስት ወደሆነችው ወደ ኢያዔል ድንኳን ሮጠ።
ሲሣራም፣ “ጠምቶኛልና እባክሽን ውሃ አጠጪኝ” አላት፤ እርሷም የወተት ዕቃውን ከፍታ የሚጠጣውን ሰጠችው፤ እንደ ገናም ሸፈነችው።
ውሃ ለመነ፤ ወተት ሰጠችው፤ ለመኳንንት በሚገባ ዕቃ፣ ርጎ አቀረበችለት።