Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



መሳፍንት 4:17

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በአሦር ንጉሥ በኢያቢስና በቄናዊው በሔቤር ጐሣ መካከል መልካም ግንኙነት ስለ ነበር ሲሣራ በእግሩ ሸሽቶ የቄናዊው የሔቤር ሚስት ወደሆነችው ወደ ኢያዔል ድንኳን ሮጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመኳንንቱም ላይ መናቅን አዘነበባቸው፤ መውጫ መግቢያው በማይታወቅ በረሓ ውስጥም አንከራተታቸው።

በፊታቸው ያለው ማእድ ወጥመድ ይሁንባቸው፤ ለማኅበራቸውም እንቅፋት ይሁን።

ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል፤ ትሑት መንፈስ ያለው ግን ክብርን ይጐናጸፋል።

አምላኬ፣ “ለክፉዎች ሰላም የላቸውም” ይላል።

ጐበዞቹ ተዋጊዎች እንኳ፣ በዚያ ቀን ዕራቍታቸውን ይሸሻሉ፤” ይላል እግዚአብሔር።

ባርቅ ግን የሲሣራን ሠረገሎችና ሰራዊቱን እስከ አሪሶት ሐጎይም ድረስ አሳደዳቸው፤ የሲሣራ ሰራዊት በሙሉ በሰይፍ ወደቀ፤ በሕይወት የተረፈ አንድም ሰው አልነበረም።

ኢያዔልም ወጥታ ሲሣራን ተቀበለችውና፣ “ጌታዬ፤ ወደ ውስጥ ግባ፤ ፈጽሞ አትፍራ” አለችው፤ ሲሣራም ወደ ድንኳኗ ገባ፤ እርሷም በልብስ ሸፍና ደበቀችው።

“የቄናዊው የሔቤር ሚስት ኢያዔል፣ ከሴቶች ሁሉ የተባረከች ትሁን፤ በድንኳን ከሚኖሩ ሴቶች ሁሉ የተባረከች ትሁን።

“በዓናት ልጅ በሰሜጋር ዘመን፣ በኢያዔል ጊዜ መንገዶች ባድማ ሆኑ፤ ተጓዦችም በጠመዝማዛ መንገድ ሄዱ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች