እነዚህ፣ እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ለቀደሙ አባቶቻቸው የሰጠውን ትእዛዞች ማክበር አለማክበራቸውን ለማወቅ ለእስራኤል መፈተኛ እንዲሆኑ እዚያው የቀሩ ነበሩ።
ከዚያም ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ እግዚአብሔር አንዲት ዛፍ አሳየው፤ ዕንጨቷንም ወደ ውሃው ጣላት፤ ውሃውም ጣፋጭ ሆነ። በዚያም እግዚአብሔር ሕግና ሥርዐት አበጀላቸው፤ በዚያም ስፍራ ፈተናቸው።
ከእናንተ መካከል እውነተኞቹ ተለይተው ይታወቁ ዘንድ፣ ይህ መለያየት በመካከላችሁ መኖሩ የግድ ነው።
ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦ “ቱሚምህና ኡሪምህ፣ ለምታምነው ሰው ይሁን፤ ማሳህ በተባለው ቦታ ፈተንኸው፤ በመሪባም ውሃ ከርሱ ጋራ ተከራከርህ።
አምላክህ እግዚአብሔር ትእዛዞቹን መጠበቅህንና በልብህ ያለውን ለማወቅ፣ ትሑት ሊያደርግህና ሊፈትንህ በእነዚህ አርባ ዓመታት በዚህ ምድረ በዳ ጕዞህ ሁሉ እንዴት እንደ መራህ አስታውስ።
ይህን የማደርገውም አባቶቻቸው እንዳደረጉት ሁሉ፣ እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን መንገድ የሚጠብቁ መሆን አለመሆናቸውን ለማወቅ እፈትናቸው ዘንድ እነርሱን መሣሪያ ለማድረግ ነው።”
በዚህ ጊዜ በከነዓን ላይ በተደረጉት ጦርነቶች ተሳትፈው የማያውቁትን እስራኤላውያን ለመፈተን፣ እግዚአብሔር ባሉበት የተዋቸው ሕዝቦች እነዚህ ናቸው፤