Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



መሳፍንት 21:3

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲህም አሉ፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ ለምን በእስራኤል ላይ ሆነ? ዛሬ ከእስራኤል አንድ ነገድ እንዴት ይታጣ?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አምላክ ሆይ፤ ለዘላለም የጣልኸን ለምንድን ነው? በማሰማሪያህ ባሉ በጎችህስ ላይ ቍጣህ ለምን ነደደ?

ታዲያ ዐላፊ አግዳሚው ፍሬዋን እንዲለቅም፣ ለምን ቅጥሯን አፈረስህ?

ሰው በራሱ ቂልነት ሕይወቱን ያበላሻል፤ በልቡ ግን እግዚአብሔርን ያማርራል።

እግዚአብሔር ሆይ፤ ከመንገድህ እንድንወጣ፣ ልባችንን በማደንደን ለምን እንዳንፈራህ አደረግኸን? ስለ ባሮችህ ስትል፣ ስለ ርስትህ ነገዶች ስትል እባክህ ተመለስ።

እግዚአብሔር ሆይ፤ ጕዳዬን በፊትህ ሳቀርብ፣ አንተ ጻድቅ መሆንህን እያወቅሁ ነው። የክፉዎች መንገድ ለምን ይሰምራል? የከዳተኞችስ ኑሮ ለምን ይሳካል?

አሕዛብም ሁሉ፣ “እግዚአብሔር በዚህች ምድር ላይ ይህን ለምን አደረገባት? ይህ አስፈሪና የሚነድድ ቍጣስ ለምን መጣባት?” ብለው ይጠይቃሉ።

ሕዝቡ ወደ ቤቴል ሄደው በዚያም እስከ ማታ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ተቀመጡ፤ ድምፃቸውንም ከፍ በማድረግ አምርረው አለቀሱ፤

በማግስቱም ጧት ሕዝቡ መሠዊያ ሠሩ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረቡ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች