እነርሱም፣ “እንግዲህ የምታደርጉት ይህ ነው፤ ወንዱን በሙሉ እንዲሁም ድንግል ያልሆኑትን ሴቶች ሁሉ ግደሉ” አሏቸው።
እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከምድያም ጋራ ተዋጉ፤ ወንዱንም በሙሉ ፈጁት፤
በዚያ ጊዜ ከተሞቹን በሙሉ ወስደን የሚኖሩባቸውን ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆቻቸውን ጭምር ፈጽመን አጠፋናቸው፤ አንዳቸውንም በሕይወት አላስቀረንም።
በኢያቢስ ገለዓድ ከሚኖረው ሕዝብ መካከል ወንድ ያልደረሰባቸው አራት መቶ ደናግል አገኙ፤ በከነዓን ምድር በሴሎ ወደሚገኘውም ሰፈር አመጧቸው።