በጦርነቱም ላይ ዐሥራ ስምንት ሺሕ ብንያማውያን ወደቁ፤ ሁሉም ምርጥ ተዋጊዎች ነበሩ።
ከብንያም ነገድ የተቈጠሩትም ሠላሳ ዐምስት ሺሕ አራት መቶ ነበሩ።
እግዚአብሔር ብንያምን በእስራኤል ፊት መታው፤ በዚያችም ዕለት እስራኤላውያን በሙሉ ሰይፍ የታጠቁ ሃያ ዐምስት ሺሕ አንድ መቶ ብንያማውያንን ገደሉ።
ብንያማውያንንም ከበቧቸው፤ አሳደዷቸው፤ ከጊብዓ በስተምሥራቅ ትይዩ ባለውም ስፍራ በቀላሉ አሸነፏቸው፤
ብንያማውያን ጀርባቸውን አዙረው በምድረ በዳው በኩል ወደ ሬሞን ዐለት በሚሸሹበት ጊዜ፣ እስራኤላውያን በመንገድ ላይ ዐምስት ሺሕ ሰው ገደሉባቸው፤ እስከ ጊድአምም ድረስ ተከታትለው ሁለት ሺሕ ሰዎች በተጨማሪ ገደሉ።