ከዚህ የተነሣ ብንያማውያን ድል መሆናቸውን ተረዱ። በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን ጊብዓ ላይ ባኖሩት ድብቅ ጦር ስለ ተማመኑ የተሸነፉ በመምሰል ለብንያማውያን ቦታ ለቀቁ።
እግዚአብሔር ብንያምን በእስራኤል ፊት መታው፤ በዚያችም ዕለት እስራኤላውያን በሙሉ ሰይፍ የታጠቁ ሃያ ዐምስት ሺሕ አንድ መቶ ብንያማውያንን ገደሉ።