ብንያማውያን ከጊብዓ ወጡ፤ በዚያችም ዕለት ከእስራኤላውያን ሃያ ሁለት ሺሕ ሰዎች ገደሉ።
“ብንያም፣ ነጣቂ ተኵላ ነው፤ ያደነውን ማለዳ ይበላል፤ የማረከውን ማታ ይከፋፈላል።”
አሁንም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ወንዶችና ሴቶች፣ ባሪያዎቻችሁ ልታደርጓቸው ትፈልጋላችሁ፤ እናንተስ ብትሆኑ ኀጢአት ሠርታችሁ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አልበደላችሁምን?
ንጉሥ በሰራዊቱ ታላቅነት አይድንም፤ ጀግናም በኀይሉ ብርታት አያመልጥም።
መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው፤ መሄጃህም በታላቅ ውሃ ውስጥ ነው፤ ዱካህ ግን አልታወቀም።
ሕዝቡን ለሰይፍ ዳረገ፤ በርስቱም ላይ እጅግ ተቈጣ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጕዳዬን በፊትህ ሳቀርብ፣ አንተ ጻድቅ መሆንህን እያወቅሁ ነው። የክፉዎች መንገድ ለምን ይሰምራል? የከዳተኞችስ ኑሮ ለምን ይሳካል?
“እስራኤል ሆይ፤ ከጊብዓ ጊዜ ጀምሮ ኀጢአት ሠራችሁ፤ በዚያም ጸናችሁ፤ በጊብዓ የነበሩትን ክፉ አድራጊዎች፣ ጦርነት አልጨረሳቸውምን?
ጠላትህን ለመውጋት ወጥተህ በሰፈርህ ጊዜ፣ ከማናቸውም ርኩሰት ራስህን ጠብቅ።
የእስራኤል ሰዎች ብንያማውያንን ለመውጋት ሄዱ፤ በጊብዓ ለሚያደርጉትም ውጊያ ቦታ ቦታቸውን ያዙ።
ይሁን እንጂ እስራኤላውያን እርስ በርሳቸው ተበረታትተው በመጀመሪያው ቀን ተሰልፈው በነበረበት ስፍራ ላይ እንደ ገና ቦታ ቦታቸውን ያዙ።
በዚሁ ጊዜም ብንያማውያን፣ እስራኤላውያንን ሊወጉ ከጊብዓ ወጡ፤ እንደ ገናም በሙሉ ሰይፍ የታጠቁ ዐሥራ ስምንት ሺሕ ሰዎች ገደሉ።