እነርሱም በኰረብታማው በኤፍሬም አገር በምትገኘው ከገዓስ ተራራ በስተሰሜን ባለችው በራሱ ርስት ላይ በተምናሔሬስ ቀበሩት።
እስራኤላውያን ድርሻ ድርሻቸውን ከያዙ በኋላ፣ ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በመካከላቸው ርስት ሰጡት፤
እግዚአብሔር ባዘዘውም መሠረት በኰረብታማው የኤፍሬም ምድር የምትገኘውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ ሰጡት፤ እርሱም ከተማዪቱን ሠራ፤ መኖሪያውም አደረጋት።
ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ባሪያ የነዌ ልጅ ኢያሱ በመቶ ዐሥር ዓመቱ ሞተ።
በኰረብታማው በኤፍሬም አገር በምትገኘው፣ ከገዓስ ተራራ በስተሰሜን ባለችው በራሱ ርስት በተምናሴራ ቀበሩት።
ኢያሱ ከሞተ በኋላ እስራኤላውያን፣ “ከነዓናውያንን ለመውጋት ማን ቀድሞ ይውጣልን?” ብለው እግዚአብሔርን ጠየቁ።
የእግዚአብሔር አገልጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ በመቶ ዐሥር ዓመቱ ሞተ።