ሚካም፣ “የየት አገር ሰው ነህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “እኔ በይሁዳ ምድር ከምትገኝ ከቤተ ልሔም የመጣሁ ሌዋዊ ነኝ፤ መኖሪያ ስፍራ እፈልጋለሁ” አለው።
ሚካም፣ “እንግዲያውስ ዐብረኸኝ ተቀመጥ፤ አባትም ካህንም ሁነኝ፤ እኔም በዓመት ዐሥር ሰቅል ብር እንዲሁም ልብስና ምግብ እሰጥሃለሁ” አለው።
በይሁዳ ምድር፣ በይሁዳ ነገድ መካከል በቤተ ልሔም የሚኖር አንድ ሌዋዊ ወጣት ነበር።
ይህም ሰው ሌላ መኖሪያ ስፍራ ለመፈለግ ከይሁዳ ቤተ ልሔም ለቅቆ ሄደ። በሚጓዝበትም ጊዜ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር ወዳለው ወደ ሚካ ቤት መጣ።