ስለዚህ ሌዋዊው ዐብሮት ለመኖር ተስማማ፤ ወጣቱም ለሚካ ከልጆቹ እንደ አንዱ ሆነለት።
ሚካም፣ “እንግዲያውስ ዐብረኸኝ ተቀመጥ፤ አባትም ካህንም ሁነኝ፤ እኔም በዓመት ዐሥር ሰቅል ብር እንዲሁም ልብስና ምግብ እሰጥሃለሁ” አለው።
ሚካም ሌዋዊውን ካህን አድርጎ አስቀመጠው፤ ወጣቱም ካህኑ ሆነ፤ በቤቱም ኖረ።
ይህም ሰው ሌላ መኖሪያ ስፍራ ለመፈለግ ከይሁዳ ቤተ ልሔም ለቅቆ ሄደ። በሚጓዝበትም ጊዜ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር ወዳለው ወደ ሚካ ቤት መጣ።