ስለዚህም ደሊላ ሳምሶንን፣ “የብርታትህን ታላቅነት ምስጢርና ታስረህ በቍጥጥር ሥር የምትውለው እንዴት እንደ ሆነ እባክህ ንገረኝ” አለችው።
አራት ጊዜም ይህንኑ ዐይነት መልእክት ላኩብኝ፤ እኔም በእያንዳንዱ ጊዜ ያንኑ መልስ ሰጠሁ።
እርስ በርሳቸው ውሸት ይነጋገራሉ፤ በሽንገላ ከንፈርና በሁለት ልብ ይናገራሉ።
የአመንዝራ ሴት አፍ ጥልቅ ጕድጓድ ነው፤ እግዚአብሔር የተቈጣውም ይገባበታል።
ሐሰተኛ ምላስ የጐዳቻቸውን ትጠላለች፤ ሸንጋይ አንደበትም ጥፋትን ታመጣለች።
ጋለሞታ ሴት ቍራሽ እንጀራ ታሳጣሃለችና፤ አመንዝራዪቱም በሕይወትህ በራሱ ላይ ትሸምቃለች።
በሚያግባቡ ቃላት አሳተችው፤ በለሰለሰ አንደበቷ አታለለችው።
የሚታመን ሰው ከምድር ጠፍቷል፤ አንድም እንኳ ቅን ሰው የለም፤ ሰው ሁሉ ደም ለማፍሰስ ያደባል፤ እያንዳንዱም ወንድሙን በመረብ ያጠምዳል።
ባልንጀራህን አትመን፤ በጓደኛህም አትታመን፤ በዕቅፍህ ለምትተኛዋ እንኳ፣ ስለምትነግራት ቃል ተጠንቀቅ።
ሚስቱም በሰርጉ በዓል ሰባት ቀን ሙሉ እያለቀሰች ጨቀጨቀችው፤ አጥብቃ ስለ ነዘነዘችውም በመጨረሻ በሰባተኛው ቀን ነገራት፤ እርሷም በበኩሏ የዕንቈቅልሹን ፍች ለሕዝቧ ነገረች።
የፍልስጥኤማውያን ገዦች ወደ እርሷ ሄደው፣ “እርሱን አስረን በቍጥጥራችን ሥር በማዋል ልናሸንፈው እንዴት እንደምንችልና የብርታቱ ታላቅነት ምስጢር ምን እንደ ሆነ እንዲያሳይሽ እስኪ አባብዪው፤ ይህን ካደረግሽ እያንዳንዳችን አንድ ሺሕ አንድ መቶ ሰቅል ጥሬ ብር እንሰጥሻለን” አሏት።
ሳምሶንም፣ “ማንም ባልደረቁ ሰባት እርጥብ ጠፍሮች ቢያስረኝ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት።