Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



መሳፍንት 16:27

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ ወንዶችና ሴቶች ቤተ ጣዖቱን ሞልተውት ነበር፤ የፍልስጥኤማውያን ገዦችም በሙሉ በዚያ ነበሩ፤ ሳምሶን ሲጫወት ለማየት ሦስት ሺሕ ያህል ወንዶችና ሴቶች በጣራው ላይ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንድ ቀን ማታ፣ ዳዊት ከዐልጋው ተነሥቶ በንጉሥ ቤት ሰገነት ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ነበር፤ ከሰገነቱ ላይ እንዳለም፣ አንዲት ሴት ገላዋን ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ በጣም ውብ ነበረች።

አዲስ ቤት በምትሠራበት ጊዜ፣ ከጣራው ላይ ሰው ወድቆ በቤትህ ላይ የደም በደል እንዳታመጣ፣ በጣራው ዙሪያ መከታ አብጅለት።

ሰላዮቹ ከመተኛታቸው በፊት ሴቲቱ ወደ ጣራው ወጥታ፣

ሳምሶን እጁን ይዞ የሚመራውን ልጅ፣ “ቤተ ጣዖቱን ደግፈው ወደ ያዙት ምሰሶዎች አስጠጋኝና ልደገፋቸው” አለው።

ሳምሶንም ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አስበኝ። አምላክ ሆይ፤ እባክህን አንድ ጊዜ ብቻ ብርታት ስጠኝና ስለ ጠፉት ዐይኖቼ ፍልስጥኤማውያንን አንዴ ልበቀላቸው።”

ሆኖም በከተማዪቱ ውስጥ ብርቱ ግንብ ስለ ነበር፣ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ፣ የከተማዪቱ ገዦችም ወደዚያ ሸሹ፤ ደጁንም በውስጥ ዘግተው ወደ ግንቡ ጣራ ወጡ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች