ከችካልም ጋራ ቸከለችው። እንደ ገናም፣ “ሳምሶን! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። ሳምሶን ከእንቅልፉ ነቃ፤ ችካሉን ከነድሩ፣ ከነሹሩባው ነቀለው።
እርሱ ብዙ ጊዜ ታደጋቸው፤ እነርሱ ግን ዐመፃን የሙጥኝ አሉ፤ በኀጢአታቸውም ተዋረዱ።
ደግሞም ደሊላ ሳምሶንን፣ “እስካሁን አሞኝተኸኛል፤ ዋሽተኸኛል። እባክህን አንተን ማሰር የሚቻለው እንዴት እንደ ሆነ ንገረኝ” አለችው። እርሱም መልሶ፣ “የራስ ጠጕሬን ሰባት ሹሩባዎች ከድር ጋራ ጐንጕነሽ በችካል ብትቸክዪው፣ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት። ደሊላም መተኛቱን አይታ ሰባቱን ሹሩባዎቹን ከድር ጋራ ጐነጐነችው፤
ከዚያም፣ “ሳታምነኝ እንዴት ‘እወድድሻለሁ’ ትለኛለህ? ስታታልለኝና የኀይልህንም ታላቅነት ምስጢር ስትደብቀኝ ይህ ሦስተኛ ጊዜህ ነው” አለችው።