ሳምሶንም፣ “ከበላተኛው መብል፣ ከብርቱም ጣፋጭ ነገር ወጣ” አላቸው። እነርሱም እስከ ሦስት ቀን ድረስ እንቈቅልሹን መፍታት አልቻሉም ነበር።
በአንተና በሴቲቱ፣ በዘርህና በዘሯ መካከል፣ ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ተረከዙን ትቀጠቅጣለህ።”
ቍራዎችም ጧትና ማታ እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፤ ውሃም ከወንዙ ይጠጣ ነበር።
ሰዎችም መጥተው ኢዮሣፍጥን፣ “ግዙፍ ሰራዊት ሊወጋህ ከሙት ባሕር ወዲያ ካለው ከኤዶም መጥቶብሃል፤ እነሆም፣ ሐሴሶን ታማር በተባለው በዓይንጋዲ ናቸው” አሉት።
ኢዮሣፍጥና ሰዎቹም ምርኳቸውን ለማጋዝ ሄዱ፤ በዚያም መካከል እጅግ ብዙ መሣሪያና ልብስ፣ ሊሸከሙ ከሚችሉትም በላይ ውድ ዕቃዎችን አገኙ። ምርኮውም ከመብዛቱ የተነሣ ለመሰብሰብ ሦስት ቀን ፈጀ።
ጥበብ ለቂል በጣም ሩቅ ናት፤ በከተማዪቱ በር ሸንጎ ላይም መናገር አይችልም።
እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ለእናንተ የመንግሥተ ሰማይን ምስጢር ማወቅ ተሰጥቷችኋል፤ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።
ጃንደረባውም፣ “የሚያስረዳኝ ሰው ሳይኖር እንዴት አድርጌ አስተውላለሁ” አለው፤ እርሱም ወደ ሠረገላው ወጥቶ ዐብሮት እንዲቀመጥ ፊልጶስን ለመነው።
ምንም አይለየንም፤ በዚህ ሁሉ በወደደን በርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
ምክንያቱም ቀላልና ጊዜያዊ የሆነው መከራችን ወደር የማይገኝለት ዘላለማዊ ክብር ያስገኝልናል።
ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በዕንጨት መስቀል ላይ ተሸከመ፤ በርሱ ቍስል እናንተ ተፈውሳችኋል።
ዕንቈቅልሹን ካልፈታችሁልኝ ግን ሠላሳ የቀጭን ፈትል በፍታ ቀሚስና ሠላሳውን የክት ልብስ እናንተ ትሰጡኛላችሁ።” እነርሱም፣ “በል ዕንቈቅልሽህን ንገረንና እንስማው” አሉት።
በአራተኛው ቀን የሳምሶንን ሚስት፣ “የዕንቈቅልሹን ፍች እንዲነግረን ባልሽን እስኪ አግባቢልን፤ አለዚያ አንቺንም የአባትሽንም ቤተ ሰብ በእሳት እናቃጥላችኋለን፤ ጠርታችሁ የጋበዛችሁን ልትዘርፉን ነው?” አሏት።