Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



መሳፍንት 1:3

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የይሁዳም ሰዎች ወንድሞቻቸውን የስምዖንን ልጆች፣ “ከነዓናውያንን ለመውጋት ድርሻችን ወደ ሆነው ምድር ዐብረን እንውጣ፤ እኛም እንደዚሁ ድርሻችሁ ወደ ሆነው ምድር ዐብረናችሁ እንወጣለን” አሏቸው፤ ስለዚህም የስምዖን ሰዎች ዐብረዋቸው ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንደ ገናም ፀንሳ ወለደች፤ እርሷም “እግዚአብሔር እንዳልተወደድኩ ሰምቶ ይህን ልጅ በድጋሚ ሰጠኝ” አለች። ከዚያም የተነሣ ስምዖን ብላ ጠራችው።

ኢዮአብም እንዲህ አለ፤ “ሶርያውያን ከበረቱብኝ አንተ መጥተህ ትረዳኛለህ፤ አሞናውያን ከበረቱብህ ደግሞ እኔ መጥቼ እረዳሃለሁ።

ሁለተኛው ዕጣ ለስምዖን ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤ ርስታቸውም ዙሪያውን በይሁዳ ነገድ ርስት የተከበበ ነበር፤

ከስምዖን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ፣ ከሌዊ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ፣ ከይሳኮር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ፣

የይሁዳ ሰዎች ከወንድሞቻቸው ከስምዖን ልጆች ጋራ ሆነው በጻፋት በሚኖሩት ከነዓናውያን ላይ ዘመቱ፤ ከተማዪቱንም ፈጽሞ ደመሰሷት፤ ስለዚህ ከተማዪቱ ሖርማ ተብላ ተጠራች።

እግዚአብሔርም፣ “ይሁዳ ቀድሞ ይውጣ፤ እነሆ ምድሪቱን በእጁ አሳልፌ ሰጥቼዋለሁ” በማለት መለሰ።

ይሁዳ በከነዓናውያንና በፌርዛውያን ላይ ወጣ፤ እግዚአብሔርም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ ቤዜቅ በተባለውም ስፍራ ዐሥር ሺሕ ሰው ገደሉ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች