Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



መሳፍንት 1:23

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የዮሴፍም ወገን ቀደም ሲል ሎዛ ትባል ወደ ነበረችው ወደ ቤቴል ከተማ ሰላዮችን በላኩ ጊዜ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያን ቦታ ቤቴል ብሎ ሰየመው፤ ቀደም ሲል ግን የከተማዪቱ ስም ሎዛ ነበር።

ያዕቆብና ዐብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ፣ በከነዓን ወደምትገኘው፣ ቤቴል ወደተባለችው ወደ ሎዛ ደረሱ።

ያዕቆብም ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ሁሉን ቻይ አምላክ በከነዓን ምድር ሎዛ በምትባል ቦታ ተገለጠልኝ፤ ባረከኝም፤

ለዮሴፍ ዝርያዎች የተመደበው ድርሻ፣ ከዮርዳኖስ ኢያሪኮ፣ ማለት ከኢያሪኮ ምንጮች በስተምሥራቅ ይነሣና፣ ምድረ በዳውን በማቋረጥ በኰረብታማው አገር አድርጎ ወደ ቤቴል ይወጣል።

ሎዛ ከምትባለው ከቤቴል ይነሣና በአጣሮት ወደሚገኘው ወደ አርካውያን ግዛት ይሻገራል፣

ከዚያ ደግሞ ወደ ደቡብ ሎዛ ማለት ወደ ቤቴል ተረተር ይሻገርና በታችኛው ቤትሖሮን በስተ ደቡብ ባለው ተራራ በኩል አድርጎ ወደ አጣሮት አዳር ይወርዳል።

ከዚያም የነዌ ልጅ ኢያሱ፣ “ሄዳችሁ ምድሪቱን፣ በተለይም የኢያሪኮን ከተማ ሰልሉ” ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር ላከ፤ ሰዎቹም ሄደው ረዓብ ከተባለች ጋለሞታ ቤት ገቡ፤ በዚያም ዐደሩ።

ኢያሱ ከቤቴል በስተምሥራቅ ካለችው ከቤትአዌን አጠገብ ወደምትገኘው ወደ ጋይ ከኢያሪኮ ሰዎችን ልኮ፣ “ወደዚያ ውጡ፤ አገሪቱንም ሰልሉ” አላቸው፤ ሰዎቹም ወጥተው ጋይን ሰለሉ።

የዮሴፍ ወገን ደግሞ ቤቴልን ወጉ፤ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋራ ነበር።

ስለዚህ ዳናውያን ምድሪቱን እንዲሰልሉና እንዲመረምሩ ዐምስት ኀያላን ሰዎች ከጾርዓና ከኤሽታኦል ከተሞች ወደዚያ ላኩ፤ እነዚህም ነገዶቻቸውን ሁሉ የሚወክሉ ነበሩ። የላኳቸውም ሰዎች፣ “ሂዱ፤ ምድሪቱን ሰልሉ” አሏቸው። መልእክተኞቹም ወደ ኰረብታማው የኤፍሬም አገር ገቡ፤ ወደሚያድሩበትም ወደ ሚካ ቤት መጡ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች