ሙሴ ባዘዘው መሠረት ኬብሮን ለካሌብ ተሰጠች፤ እርሱም ሦስቱን የዔናቅ ልጆች ከውስጧ አሳደደ።
በኔጌብ በኩል ዐልፈው አኪመን፣ ሴሲና ተላሚ የተባሉ የዔናቅ ዝርያዎች ወደሚኖሩበት ወደ ኬብሮን መጡ። ኬብሮን የተመሠረተችው ጣኔዎስ በግብጽ ምድር ከመቈርቈሯ ሰባት ዓመት አስቀድሞ ነበር።
አገልጋዬ ካሌብ ግን የተለየ መንፈስ ስላለውና በፍጹም ልቡ የተከተለኝ በመሆኑ ሄዶባት ወደ ነበረችው ምድር አስገባዋለሁ፤ ዘሮቹም ይወርሷታል።
ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ በቀር የሚያያት የለም፤ እርሱ ያያታል፤ እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ ስለ ተከተለ፣ የረገጣትን ምድር ለርሱና ለዘሮቹ እሰጣለሁ።”
ከዚያም ኢያሱና ከርሱ ጋራ የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከዔግሎን ወደ ኬብሮን ወጡ፤ ወጓትም።
በዚያ ጊዜ ኢያሱ ሄዶ በተራራማው አገር፣ ማለት በኬብሮን፣ በዳቤርና በዓናብ እንዲሁም በመላው የይሁዳና የእስራኤል ተራራማ አገሮች ያሉትን የዔናቅን ዘሮች ከነከተሞቻቸው በሙሉ ደመሰሳቸው።
ኬብሮን ቀድሞ ከዔናቃውያን ሁሉ ታላቅ በሆነው ሰው በአርባቅ ስም ቂርያት አርባቅ ተብላ ትጠራ ነበር። ከዚያም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።
ቀደም ሲል ቂርያት አርባቅ ተብላ በምትጠራው በኬብሮን በሚኖሩት ከነዓናውያን ላይ ዘመቱ፤ ሴሲንን፣ አኪመንንና ተላሚንን ድል አደረጉ።