ስለዚህ ኢያሱ ጋይን አቃጠላት፤ እስከ ዛሬ እንደሚታየውም ለዘላለም የዐመድ ቍልልና ባድማ አደረጋት።
“ ‘ይህን ቀድሞ እንደ ወሰንሁት፣ አልሰማህምን? ጥንትም እንዳቀድሁት፣ አሁን ግን እንዲፈጸም አደረግሁት፤ ይህም የተመሸጉትን ከተሞች፣ አንተ የድንጋይ ክምር ማድረግህ ነው።
ስለ ደማስቆ የተነገረ ንግር፤ “እነሆ፤ ደማስቆ ከእንግዲህ ከተማነቷ ይቀራል፤ የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች።
ከተማዪቱን የድንጋይ ክምር አድርገሃታል፤ የተመሸገችውንም ከተማ አፈራርሰሃታል፤ የተመሸገችው የባዕድ ከተማ ከእንግዲህ አትኖርም፤ ተመልሳም አትሠራም።
ስለዚህ በአሞናውያን ከተማ በረባት ላይ፣ የጦርነት ውካታ ድምፅ የሚሰማበት ጊዜ ይመጣል፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “እርሷም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ በዙሪያዋ ያሉት መንደሮችም ይቃጠላሉ፤ እስራኤልም ከአገሯ ያስወጧትን፣ ከአገሯ ታስወጣለች፤” ይላል እግዚአብሔር፤
ከሩቅ መጥታችሁ በርሷ ላይ ውጡ፤ ጐተራዎቿን አፈራርሱ፤ እንደ እህል ክምር ከምሯት፤ ፈጽማችሁ አጥፏት፤ ምኗም አይቅር።
“ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር፣ የቀበሮም ጐሬ አደርጋታለሁ፤ የይሁዳንም ከተሞች፣ ሰው የማይኖርባቸው ባድማ አደርጋቸዋለሁ።”
ስለዚህ በእናንተ ምክንያት፣ ጽዮን እንደ ዕርሻ ትታረሳለች፣ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ የቤተ መቅደሱም ኰረብታ ዳዋ የወረሰው ጕብታ ይሆናል።
በከተማዪቱ የተገኘውን የምርኮ ዕቃ ሁሉ በአደባባይዋ መካከል ላይ ሰብስበህ፣ ከተማዪቱን ከነምርኮዋ እንዳለ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ በሙሉ አቃጥል። ለዘላለም እንደ ፈረሰች ትቅር፤ ተመልሳም አትሠራ።
እግዚአብሔር ከብርቱ ቍጣው ይመለስ ዘንድ ዕርም ነገሮች በእጅህ አይገኙ፤ እርሱ ምሕረቱን ያሳይሃል፤ ይራራልሃል፤ ለአባቶችህ በመሐላ ተስፋ በሰጠው መሠረት ቍጥርህን ያበዛዋል፤
ኢያሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ካህናት ቆመውበት በነበረው በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድንጋዮችን አቆመ፤ እነዚህም ድንጋዮች እስከ ዛሬ ድረስ በዚሁ ስፍራ ይገኛሉ።
የጋይንም ንጉሥ በዛፍ ላይ ሰቀለው፤ ሬሳውንም እስኪመሽ ድረስ እዚያው እንዳለ ተወው፤ ፀሓይ ስትጠልቅም፣ ኢያሱ ሬሳውን እንዲያወርዱትና በከተማው በር ላይ እንዲጥሉት አዘዘ፤ የትልልቅ ድንጋይ ቍልልም ከመሩበት፤ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ እዚያው ይገኛል።