የሌዊ ልጅ የቀዓት ጐሣዎች ለሆኑት ለሌሎቹ ደግሞ ከኤፍሬም ነገድ ላይ ተከፍለው የሚከተሉት ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው።
ልጁ ቡቂ፣ ልጁ ኦዚ፣ ልጁ ዘራእያ፣
ለአንዳንድ የቀዓት ጐሣዎችም ከኤፍሬም ነገድ ድርሻ ላይ የሚኖሩበት ከተማ ተሰጣቸው።
ለካህናቱ ለአሮን ዝርያዎች ከነመሰማሪያቸው የተሰጧቸው ከተሞች ዐሥራ ሦስት ነበሩ።
ለቀሩት ለቀዓት ዘሮች ደግሞ ከኤፍሬምና ከዳን ነገድ ጐሣዎች፣ እንዲሁም ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ጐሣዎች ዐሥር ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው።