ደግሞም እስከ ባዕላትብኤር ወይም ኔጌብ ውስጥ እስካለው እስከ ራሞት ድረስ ባሉት ከተሞች ዙሪያ የሚገኙት መንደሮች ሁሉ ከእነዚሁ ጋራ ይጠቃለላሉ። እንግዲህ በየጐሣው የተደለደለው የስምዖን ነገድ ርስት ይህ ነበር።
በእነዚህም ከተሞች ዙሪያ እስከ ባኣል የሚዘልቁ መንደሮች ነበሩ፤ መኖሪያቸው በዚሁ ሲሆን። የትውልድ መዝገብም አላቸው።
ዓይን፣ ሪሞን፣ ዔቴርና ዓሻን የተባሉት አራት ከተሞቻቸውና መንደሮቻቸው፣
የይሁዳ ነገድ የያዘው ርስት እጅግ ሰፊ ስለ ነበር፣ ከይሁዳ ነገድ ድርሻ ተከፍሎ ለስምዖን ነገድ በርስትነት ተሰጠ። ከዚህ የተነሣም የስምዖን ነገድ በይሁዳ ነገድ ድርሻ ርስት ሊካፈል ቻለ።
ይህንም፣ በቤቴል፣ በደቡብ ራሞትና በየቲር ለነበሩ፣