እነዚህ ለንፍታሌም ነገድ ርስት ሆነው በየጐሣው የተደለደሉ ከተሞችና መንደሮች ነበሩ።
ቤን ሃዳድም የንጉሥ አሳን ሐሳብ ተቀብሎ፣ የጦር አዛዦቹን በእስራኤል ከተሞች ላይ አዘመተ፤ እርሱም ዒዮንን፣ ዳንን፣ አቤል ቤት ማዕካን እንዲሁም ንፍታሌምን ጨምሮ ኪኔሬትን በሙሉ ድል አድርጎ ያዘ።
የንፍታሌም ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የአሴርን ምድር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያዋስናል።
ይርኦን፣ ሚግዳልኤል፣ ሖሬም፣ ቤትዓናትና ቤትሳሚስ። እነዚህ ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ ዘጠኝ ከተሞች ናቸው።
ሰባተኛው ዕጣ ለዳን ነገድ በየጐሣው ወጣ፤