ድንበራቸውም ከሔሌፍና በጻዕናይም ካለው ከትልቁ የወርካ ዛፍ ይነሣና በአዳሚኔቄብና በየብኒኤል ዐልፎ ወደ ለቁም በመምጣት ዮርዳኖስ ላይ ይቆማል፤
ስድስተኛው ዕጣ ለንፍታሌም ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤
ድንበሩ በአዝኖት ታቦር ያልፍና ወደ ምዕራብ በመታጠፍ ሑቆቅ ላይ ይቆማል፤ ይኸው ድንበር በደቡብ ዛብሎንን፣ በምዕራብ አሴርን፣ በምሥራቅ ዮርዳኖስን ይነካል።
በዚያ ጊዜ ቄናዊው ሔቤር፣ የሙሴ ዐማች የኦባብ ልጆች ከሆኑት ከሌሎቹ ቄናውያን ተለይቶ በቃዴስ አጠገብ ጻዕናይም ከተባለ ቦታ ከሚገኘው ትልቅ ወርካ ጥግ ድንኳኑን ተክሎ ነበር።