እነዚህ ለይሳኮር ነገድ ርስት ሆነው ለየጐሣ ለየጐሣው የተደለደሉ ከተሞችና መንደሮቻቸው ነበሩ።
ድንበራቸውም ታቦርና፣ ሻሕጹማን፣ ቤትሳሚስን ይነካና በዮርዳኖስ ላይ ያቆማል። እነዚህ ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ ስድስት ከተሞች ናቸው።
ዐምስተኛ ዕጣ ለአሴር ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤