Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ኢያሱ 18:19

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ሰሜናዊውን የቤትሖግላንን ተረተር ዐልፎ ይሄድና በስተ ደቡብ የዮርዳኖስ ወንዝ እስከሚገባበት እስከ ጨው ባሕር ወሽመጥ ይዘልቃል፤ ይህም ደቡባዊ ድንበሩ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነዚህ የኋለኞቹ ዐምስቱ ነገሥታት በሲዲም ሸለቆ፣ በጨው ባሕር ተሰበሰቡ።

እነዚያንም ከተሞችና ረባዳውን ምድር በሙሉ፣ በከተሞቹም የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ፣ የምድሩን ቡቃያ ሳይቀር ገለባበጠው።

እግዚአብሔር በሚጋረፍም ነፋስ፣ የግብጽን ባሕረ ሰላጤ ያደርቃል፤ እጁን በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ይዘረጋል፤ ሰባት ታናናሽ ጅረትም አድርጎ ይለያየዋል፤ ስለዚህ ሰዎች ከነጫማቸው መሻገር ይችላሉ።

“ ‘የደቡብ ድንበራችሁ በኤዶም ወሰን ላይ ካለው ከጺን ምድረ በዳ ጥቂቱን ይጨምራል፤ በምሥራቅም በኩል የደቡብ ድንበራችሁ ከጨው ባሕር ጫፍ ይጀምርና

የምዕራቡ ወሰን፣ በዓረባ የሚገኘው ዮርዳኖስ ሲሆን፣ ይኸውም ከፈስጋ ተረተሮች በታች፣ ከኪኔሬት አንሥቶ የጨው ባሕር እስከሚባለው እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ ነው።

እንዲሁም ከኪኔሬት ባሕር እስከ ጨው ባሕር ያለውን ምሥራቃዊውን ዓረባ፣ እስከ ቤትየሺሞትና ከዚያም በስተ ደቡብ እስከ ፈስጋ ተራራ ግርጌ ድረስ ገዝቷል።

የደቡብ ወሰናቸው፣ ከጨው ባሕር ደቡባዊ ጫፍ ካለው የባሕር ወሽመጥ ይነሣል፤

ወደ ቤትዓረባ ሰሜናዊ ተረተር በመቀጠል ቍልቍል ወደ ዓረባ ይወርዳል።

በምሥራቅ በኩል ያለው ድንበር፣ ራሱ የዮርዳኖስ ወንዝ ነው። ይህ እንግዲህ የብንያም ነገድ ጐሣዎች በርስትነት የወረሷት ምድር ዳር ድንበሮቿ ሁሉ እነዚህ ነበሩ።

ከላይ የሚወርደው ውሃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ “አዳም” ተብላ እስከምትጠራው ሩቅ ከተማ ድረስ በመከማቸት እንደ ክምር ተቈለለ፤ ቍልቍል ወደ ዓረባ ጨው ባሕር የሚወርደውም ውሃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም ከኢያሪኮ ትይዩ ባለው አቅጣጫ ተሻገሩ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች