ሰለጰዓድ የአፌር ልጅ፣ የገለዓድ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የምናሴ ልጅ ነው። እርሱም ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም። የሴቶች ልጆቹም ስም ማህለህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካ፣ ቲርጻ ይባላል።
የኤፍሬምንም የልጅ ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ ድረስ አየ። የምናሴ ልጅ ማኪር የወለዳቸውም ልጆች በዮሴፍ ጭን ላይ ተወለዱ።
የአፌር ልጅ ሰለጰዓድ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ ልጆቹ ሴቶች ብቻ ነበሩ፤ እነርሱም ማህለህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካና ቲርጻ ይባላሉ።
የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የገለዓድ ልጅ፣ የአፌር ልጅ፣ የሰለጰዓድ ሴት ልጆች ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ጐሣዎች ነበሩ፤ ስማቸውም ማህለህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካና ቲርጻ ይባላል። እነርሱም፣
ስለዚህ ይህ ርስት ለተቀሩት የምናሴ ዘሮች ማለትም ለአቢዔዝር፣ ለኬሌግ፣ ለአሥሪኤል፣ ለሴኬም፣ ለአፌር፣ ለሸሚዳ ጐሣዎች የተሰጠ ነው፤ እነዚህ በየጐሣዎቻቸው የዮሴፍ ልጅ የምናሴ ሌሎች ወንዶች ዝርያዎች ናቸው።