Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ኢያሱ 16:8

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ድንበሩ አሁንም ከታጱዋ በምዕራብ በኩል አድርጎ ወደ ቃና ወንዝ ይወርድና ከባሕሩ ላይ ይቆማል። እንግዲህ የኤፍሬም ነገድ በየጐሣ በየጐሣቸው የተካፈሉት ርስት ይህ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱንም በገለዓድ፣ በአሴር፣ በኢይዝራኤል፣ በኤፍሬምና በብንያም እንዲሁም በእስራኤል ሁሉ ላይ አነገሠው።

ምድራቸውና መኖሪያቸው ቤቴልንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ከተሞች፣ በስተምሥራቅ ነዓራን፣ በስተ ምዕራብ ጌዝርንና መንደሮቿን፣ እንዲሁም ሴኬምንና መንደሮቿን፣ ከዚያም ዐልፎ ጋያንና መንደሮቿን በሙሉ ያጠቃልል ነበር።

የኤፍሬም ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የምናሴን ምድር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያዋስናል።

የምዕራቡ ድንበራችሁ ደግሞ የታላቁ ባሕር ዳርቻ ይሆናል። በምዕራቡ በኩል ያለው ወሰናችሁም ይኸው ነው።

የታጱዋ ንጉሥ፣ አንድ የኦፌር ንጉሥ፣ አንድ

ይህም በምናሴ ነገድ ርስት ውስጥ ለኤፍሬም ዘሮች የተመደቡትን ከተሞች በሙሉና መንደሮቻቸውን የሚያጠቃልል ነው።

የምናሴ ርስት ከአሴር አንሥቶ ከሴኬም በስተምሥራቅ እስካለችው እስከ ሚክምታት ይደርሳል፤ ድንበሩም ወደ ደቡብ በመዝለቅ በዓይንታጱዋ የሚኖረውን ሕዝብ ይጨምራል።

በመቀጠልም ወደ ዔብሮን፣ ወደ ረአብ፣ እንዲሁም ወደ ሐሞንና ወደ ቃና ሽቅብ ወጥቶ እስከ ታላቁ ሲዶና ይደርሳል።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች