እስከ ባሕሩ ይዘልቃል። በስተሰሜን ደግሞ ከሚክምታት ተነሥቶ በምሥራቅ በኩል ወደ ተአናት ሴሎ ይታጠፍና ከዚያ በማለፍ እስከ ኢያኖክ ምሥራቅ ይዘልቃል።
ከኢያኖክም በመነሣት ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ቍልቍል ይወርድና በኢያሪኮ በኩል አድርጎ ዮርዳኖስ ላይ ብቅ ይላል።
የምናሴ ርስት ከአሴር አንሥቶ ከሴኬም በስተምሥራቅ እስካለችው እስከ ሚክምታት ይደርሳል፤ ድንበሩም ወደ ደቡብ በመዝለቅ በዓይንታጱዋ የሚኖረውን ሕዝብ ይጨምራል።
መላው የእስራኤላውያን ማኅበር በሴሎ ተሰበሰቡ፣ የመገናኛውንም ድንኳን እዚያው ተከሉ፤ ምድሪቱም ጸጥ ብላ ተገዛችላቸው።