ከዚያም በመቀጠል ከተራራው ዐናት ተነሥቶ ወደ ኔፍቶ ምንጮች በማምራት፣ በዔፍሮን ተራራ ላይ ያሉትን ከተሞች ዐልፎ ይወጣና ቂርያትይዓይሪም ተብሎ ወደሚጠራው ወደ በኣላ ቍልቍል ይወርዳል።
እርሱና ዐብረውት ያሉት ሰዎች ሁሉ በታቦቱ ላይ ባለው ኪሩቤል ላይ በተቀመጠው በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔርም ስም የተጠራውን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ለማምጣት በይሁዳ ወዳለችው ወደ ባኣላ ሄዱ።
ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ በኪሩብና በኪሩብ መካከል የተቀመጠውን ስሙም በርሱ የተጠራውን፣ የእግዚአብሔር አምላክን ታቦት ከዚያ ለማምጣት በይሁዳ ወዳለችው ቂርያትይዓይሪም ወደተባለችው ወደ በኣላ ሄዱ።
በኣላ፣ ዒዪም፣ ዔጼም፣
ቂርያትይዓይሪም የተባለችው ቂርያትበኣልና ረባት፤ እነዚህም ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
በስተ ደቡብ ያለው ድንበር ደግሞ በምዕራብ በኩል ከቂርያትይዓይሪም ጥግ ይነሣና እስከ ኔፍቶ ውሃ ምንጭ ይዘልቃል፤
ስለዚህ እስራኤላውያን ተጕዘው በሦስተኛው ቀን ገባዖን፣ ከፊራ፣ ብኤሮትና ቂርያትይዓይሪም ወደተባሉት የገባዖን ሰዎች ወደሚኖሩባቸው ከተሞች መጡ።
ወጥተውም በይሁዳ ምድር ባለችው በቂርያትይዓሪም ሰፈሩ፤ እንግዲህ ከቂርያትይዓይሪም በስተ ምዕራብ ያለው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ የዳን ሰፈር መባሉ ከዚሁ የተነሣ ነው።
ከዚያም ወደ ቂርያትይዓይሪም ሰዎች መልእክተኞች ልከው፣ “ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት መልሰውልናል፤ ውረዱና ይዛችሁ ወደ ሰፈራችሁ ውጡ” አሏቸው።