ዚፍ፣ ጤሌም፣ በዓሎት፣
የይረሕምኤል ወንድም የካሌብ ወንዶች ልጆች፤ የበኵር ልጁ ሞሳ ሲሆን፣ እርሱም ዚፍን ወለደ፤ ዚፍም መሪሳን ወለደ፤ መሪሳም ኬብሮንን ወለደ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ በስምህ አድነኝ፤ በኀይልህም ፍረድልኝ።
ቃዴስ፣ ሐጾር፤ ዩትናን፣
ሐጾርሐዳታ፣ ሐጾር የምትባለው ቂርያትሐጾር
ስለዚህ ሳኦል ሰዎቹን ጥላኢም በተባለ ቦታ ሰብስቦ ቈጠራቸው፤ እነርሱም ሁለት መቶ ሺሕ እግረኛ ወታደሮችና ከይሁዳም ዐሥር ሺሕ ሰዎች ነበሩ፤
ዳዊት በምድረ በዳ ባሉ ምሽጎችና በዚፍ ምድረ በዳ ኰረብቶች ተቀመጠ፤ ሳኦልም በየዕለቱ ይከታተለው ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ዳዊትን አሳልፎ አልሰጠውም።
የዚፍ ሰዎች ወደ ጊብዓ ወደ ሳኦል ወጥተው እንዲህ አሉ፤ “እነሆ፤ ዳዊት ከየሴሞን በስተ ደቡብ በኤኬላ ኰረብታ ላይ በሖሬሽ ምሽጎች ውስጥ በመካከላችን ተደብቆ የለምን?
ስለዚህ ሰዎቹ ለመሄድ ተነሥተው ከሳኦል በፊት ወደ ዚፍ ሄዱ፤ በዚህ ጊዜ ዳዊትና ሰዎቹ ከየሴሞን በስተ ደቡብ በዓረባ ውስጥ ባለው በማዖን ምድረ በዳ ነበሩ።