ለይሁዳ ነገድ በየጐሣቸው የተሰጣቸው ርስት ይህ ነው፤
ስለ ይሁዳ የተናገረው ይህ ነው፦ “እግዚአብሔር ሆይ፤ የይሁዳን ጩኸት ስማ፤ ወደ ወገኖቹም አምጣው። በገዛ እጆቹ ራሱን ይከላከላል፤ አቤቱ ከጠላቶቹ ጋራ ሲዋጋ ረዳቱ ሁን!”
እርሷም፣ “እባክህ፤ ባርከኝ፤ በኔጌብ መሬት እንደ ሰጠኸኝ ሁሉ፣ አሁንም የውሃ ምንጭ ጕድጓዶች ስጠኝ” አለችው፤ ካሌብም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጮች ሰጣት።
በኔጌብ አካባቢ በኤዶም ድንበር ላይ በወሰኑ ጫፍ የሚገኙት የይሁዳ ነገድ ደቡባዊ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ቀብጽኤል፣ ዔዴር፣ ያጉር፣