እነዚህ ሁሉ ነገሥታት እስራኤልን ለመውጋት ኀይላቸውን አስተባብረው በማሮን ውሃ አጠገብ በአንድነት ሰፈሩ።
ሶርያውያን በእስራኤላውያን እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ፣ እንደ ገና ተሰባሰቡ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶቼ ምንኛ በዙ! ስንቱስ በእኔ ላይ ተነሣ!
አይተውም ተደነቁ፤ ደንግጠውም ፈረጠጡ።
እናንተ አሕዛብ፣ ፎክሩ፤ ነገር ግን ደንግጡ! በሩቅ አገር ያላችሁ አድምጡ። ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤ ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤
እነዚህም ሰራዊታቸውን ሁሉ እጅግ ብዙ ከሆኑ ፈረሶችና ሠረገሎች ጋራ ይዘው ወጡ፤ የሰራዊቱም ብዛት በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ነበር።
እግዚአብሔር ኢያሱን፣ “እነዚህን ሁሉ ነገ በዚች ሰዓት እንደ ሙት አድርጌ፣ በእስራኤል እጅ አሳልፌ ስለምሰጣቸው አትፍራቸው። የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሠረገሎቻቸውንም ታቃጥላለህ” አለው።
ኢያሱንና እስራኤልን ለመውጋት በአንድነት መጡ።
እነርሱም ምልክቶች የሚያደርጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸው፤ ሁሉን በሚችል አምላክ ታላቅ ቀን ለሚሆነው ጦርነት እንዲሰበስቧቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይሄዳሉ።