ኢያሱ እነዚህን የነገሥታት ከተሞች በሙሉና ነገሥታታቸውን ሁሉ ያዘ፤ በሰይፍም ስለት ፈጃቸው፤ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ባዘዘውም መሠረት ፈጽሞ ደመሰሳቸው።
አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ አሳልፎ በሰጠህና አንተም ድል ባደረግሃቸው ጊዜ፣ ሁሉንም ፈጽመህ ደምስሳቸው፤ ከእነርሱ ጋራ ቃል ኪዳን እንዳታደርግ፤ አትራራላቸውም።
ይሁን እንጂ እንደሚባላ እሳት ከፊትህ ቀድሞ የሚሻገረው አምላክህ እግዚአብሔር መሆኑን ዛሬ ርግጠኛ ሁን፤ እነርሱን ያጠፋቸዋል፤ በፊትህም ድል ያደርጋቸዋል፤ አንተም እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት ታስወጣቸዋለህ፤ በፍጥነትም ትደመስሳቸዋለህ።
ስለዚህ ኢያሱና እስራኤላውያን እስከ መጨረሻው ደመሰሷቸው፤ የተረፉት ጥቂቶቹ ግን ወደ ተመሸጉት ከተሞቻቸው ለመድረስ ቻሉ።
በዚያች ዕለት ኢያሱ መቄዳን ያዘ፤ ከተማዪቱንና ንጉሧንም በሰይፍ ስለት መታ፤ አንድም ሰው ሳያስቀር በውስጧ ያለውን ሁሉ ፈጽሞ ደመሰሰ፤ በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ያደረገውንም ሁሉ፣ በመቄዳ ንጉሥ ላይ አደረገ።
እንዲሁም እግዚአብሔር ከተማዪቱንና ንጉሥዋን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። ኢያሱ ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ በሰይፍ ስለት አጠፋ፤ አንድም ሰው አላስተረፈም። በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ያደረገውንም በልብና ንጉሥ ላይ ደገመው።
እግዚአብሔር ለኪሶን አሳልፎ ለእስራኤል ሰጠ፤ ኢያሱም በሁለተኛው ቀን ያዛት፤ በልብና እንዳደረገው ሁሉ እዚህም ከተማዪቱንና በውስጧ ያሉትን ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጃቸው።
በዚያ ዕለት ያዟት፤ በሰይፍም ስለት አጠፏት፤ በለኪሶ እንዳደረጉት ሁሉ እዚህም በውስጧ የሚገኙትን ፈጽመው ደመሰሷቸው።
ከተማዪቱንም ከንጉሧ፣ ከመንደሮቿና በውስጧ ካሉት ጋራ ሁሉ አንድም ሰው ሳያስቀሩ በሰይፍ ስለት ፈጇቸው፤ በዔግሎን እንዳደረጉት ሁሉ እዚህም ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ ፈጽመው ደመሰሱ።
ያም ሆኖ ግን ኢያሱ ካቃጠላት ከአሦር በቀር፣ እስራኤላውያን በየተራራው ላይ ያሉትን ከተሞች አላቃጠሉም ነበር።
እግዚአብሔር ባሪያውን ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ፣ ሙሴም ኢያሱን አዘዘው፤ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ካዘዘው ሁሉ እርሱ ያልፈጸመው አንዳች ነገር አልነበረም።
“ከሊባኖስ እስከ ማስሮን ባለው ተራራማ ምድር ላይ የሚኖሩትን ሁሉ፣ ሲዶናውያንንም ጭምር እኔው ራሴ ከእስራኤላውያን ፊት አሳድጄ አስወጣቸዋለሁ። ብቻ አንተ ባዘዝሁህ መሠረት ምድሪቱን ርስት አድርገህ ለእስራኤላውያን አካፍል።
እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው፤ አንድም ጠላት ሊቋቋማቸው አልቻለም፤ እግዚአብሔር ጠላቶቻቸውን ሁሉ አሳልፎ በእጃቸው ሰጥቷቸዋልና።
መሠዊያውንም የሠራው የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ፣ እስራኤላውያንን ባዘዛቸው መሠረት ሲሆን፣ ይህንም የሠራው በሙሴ የሕግ መጽሐፍ እንደ ተጻፈው ባልተጠረበና የብረት መሣሪያ ባልነካው ድንጋይ ነው፤ በዚህም ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ፤ የኅብረት መሥዋዕትም ሠዉ።
ከተማዪቱን ስትይዙም በእሳት አቃጥሏት፤ እግዚአብሔር ያዘዘውንም አድርጉ፤ እነሆ አዝዣችኋለሁ።”
እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፤ “አምላክህ እግዚአብሔር ባሪያውን ሙሴን እንዳዘዘው፣ ምድሪቱን በሙሉ ለእናንተ እንደሚሰጣችሁና ነዋሪዎቿንም ከፊታችሁ እንደሚያጠፋቸው በርግጥ ለእኛ ለባሪያዎችህ ተነግሮናል፤ ስለዚህ ከእናንተ የተነሣ ለሕይወታችን በመሥጋት ይህን አድርገናል።