ከዚህ በኋላ ኢያሱ ከመላው እስራኤላውያን ጋራ ጌልገላ ወዳለው ሰፈር ተመለሰ።
በኢየሩሳሌም ዙሪያ የራሳቸውን መንደሮች ሠርተው ስለ ነበር፣ መዘምራኑን ያመጧቸው ከቤትጌልገላ፣ ከጌባዕና ከዓዝሞት አካባቢ ነው።
ከዚያም ኢያሱ ከመላው እስራኤል ጋራ ጌልገላ ወዳለው ሰፈር ተመለሰ።
ኢያሱ እነዚህን ሁሉ ነገሥታትና ምድራቸውን ያሸነፈው በአንድ ዘመቻ ብቻ ነበር፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተዋግቶላቸዋልና።
የአሦር ንጉሥ ኢያቢስ ይህን በሰማ ጊዜ፣ ወደ ማዶን ንጉሥ፣ ወደ ዮባብ ንጉሥ፣ ወደ ሺምሮን ንጉሥ፣ ወደ አዚፍ ንጉሥ ላከ።
የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን ሕዝቡ ዮርዳኖስን ተሻግሮ በኢያሪኮ ምሥራቃዊ ዳርቻ በጌልገላ ሰፈረ።
ከዚያም ሳሙኤል ሕዝቡን፣ “ኑና ወደ ጌልገላ እንሂድ፤ ንግሥናውን እናጽና” አለ።