ሰውየውም፣ “ጌታዬ፤ አምንበት ዘንድ እርሱ ማን ነው?” ሲል ጠየቀው።
አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፤ ውድሽ ከሌሎች እንዴት ቢበልጥ ነው? እስከዚህ የምትማጠኚንስ፣ ውድሽ ከሌሎች እንዴት ቢበልጥ ነው?
“ይመጣል ተብሎ የሚጠበቀው አንተ ነህ? ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” ሲል ጠየቀ።
ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉት አየና፣ “ምን ትፈልጋላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “ረቢ፣ የት ትኖራለህ?” አሉት፤ “ረቢ” ማለት መምህር ማለት ነው።
ኢየሱስም፣ “አይተኸዋል፤ አሁንም ከአንተ ጋራ የሚነጋገረው እርሱ ነው” አለው።
ታዲያ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ስለ እርሱስ ሳይሰሙ እንዴት ያምኑበታል? ሰባኪ ሳይኖር እንዴት መስማት ይችላሉ?