እነርሱም፣ “ጌታ ሆይ፤ እንግዲያውስ ይህን እንጀራ ሁልጊዜ ስጠን” አሉት።
ብዙዎች፣ “አንዳች በጎ ነገር ማን ያሳየናል?” ይላሉ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የፊትህ ብርሃን በላያችን ይብራ።
ሴትዮዋም፣ “ጌታዬ፤ እንዳልጠማና ውሃ ለመቅዳት እንዳልመላለስ፣ እባክህ ይህን ውሃ ስጠኝ” አለችው።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ የምትፈልጉኝ እንጀራ ስለ በላችሁና ስለ ጠገባችሁ እንጂ፣ ታምራዊ ምልክቶችን ስላያችሁ አይደለም።
ለዘላለም የተመሰገነው የጌታ የኢየሱስ አምላክና አባት እንደማልዋሽ ያውቃል።