አባቶቻችን በዚህ ተራራ ላይ ሰገዱ፤ እናንተ አይሁድ ግን ሰው መስገድ ያለበት በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ” አለችው።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “በፊቴ ያቀረብኸውን ጸሎትና ልመና ሰምቻለሁ፤ ይህን የሠራኸውንም ቤተ መቅደስ፣ ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ቀድሼዋለሁ፤ ዐይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ።
ዳዊትም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረበ። እግዚአብሔርንም ጠራ፤ እግዚአብሔርም የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ከሰማይ በእሳት መለሰለት።
ከዚያም ዳዊት፣ “ከእንግዲህ የእግዚአብሔር አምላክ ቤት በዚህ ይሆናል፤ እንዲሁም ስለ እስራኤል የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበት መሠዊያ በዚሁ ይቆማል” አለ።
አሁን ግን ስሜ በዚያ እንዲሆን ኢየሩሳሌምን፣ ሕዝቤን እስራኤልን እንዲገዛም ዳዊትን መርጫለሁ።’
እግዚአብሔር ለሰሎሞን በሌሊት ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ ይህንም ስፍራ መሥዋዕት የሚቀርብበት ቤተ መቅደስ እንዲሆን ለራሴ መርጬዋለሁ።
ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤተ መቅደስ መርጫለሁ፤ ቀድሼዋለሁም። ዐይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ።
እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና፣ ማደሪያውም ትሆን ዘንድ ወድዷልና እንዲህ አለ፤
ነገር ግን የይሁዳን ነገድ፣ የወደዳትን የጽዮንን ተራራ መረጠ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤ ታዲያ ቤት የት ትሠሩልኛላችሁ? ይላል ጌታ፤ ወይስ ማረፊያ የሚሆነኝ ቦታ የት ነው?
ሕዝቡ ግን ወደ ኢየሩሳሌም እያመራ መሆኑን ስላወቁ አልተቀበሉትም።
ለመሆኑ አንተ፣ ይህን ጕድጓድ ከሰጠን፣ ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን? እርሱ ራሱና ልጆቹ፣ እንስሳቱም ከዚሁ ጕድጓድ ጠጥተዋል።”
ልትወርሳት ወደምትሄድባት ምድር አምላክህ እግዚአብሔር በሚያስገባህ ጊዜ በረከቱን በገሪዛን ተራራ፣ መርገሙን ደግሞ በጌባል ተራራ ላይ ታሰማለህ።
ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዮሴፍና ብንያም ሕዝቡን ለመባረክ በገሪዛን ተራራ ላይ ይቁሙ።