ዳሩ ግን ያጠመቀው ኢየሱስ ሳይሆን ደቀ መዛሙርቱ ነበሩ።
ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ተጠርተው ነበር።
ከዚህ በኋላ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ይሁዳ አገር ሄዱ፤ እዚያም ከእነርሱ ጋራ ጥቂት ተቀመጠ፤ አጠመቀም።
ወደ ዮሐንስም መጥተው፣ “ረቢ፤ በዮርዳኖስ ማዶ ከአንተ ጋራ የነበረው፣ ስለ እርሱም የመሰከርህለት ሰው እነሆ፤ ያጠምቃል። ሰውም ሁሉ ወደ እርሱ እየሄደ ነው” አሉት።
ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁ አዘዛቸው። ከዚህ በኋላ፣ ጴጥሮስ ጥቂት ቀን ከእነርሱ ጋራ እንዲቀመጥ ለመኑት።