እውነት እላችኋለሁ፤ የስንዴ ቅንጣት መሬት ላይ ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች።
ሥሩ በምድር ውስጥ ቢያረጅ፣ ጕቶው በመሬት ውስጥ ቢበሰብስም፣
ጕልበቴ እንደ ገል ደረቀ፤ ምላሴ ከላንቃዬ ጋራ ተጣበቀ፤ ወደ ሞት ዐፈርም አወረድኸኝ።
በምድሪቱ ላይ እህል ይትረፍረፍ፤ በተራሮችም ዐናት ላይ ይወዛወዝ። ፍሬው እንደ ሊባኖስ ይንዠርገግ፤ በከተማ ያለውም እንደ ሜዳ ሣር እጅብ ብሎ ይውጣ።
እንጀራን ለመጋገር እህል ይፈጫል፤ ስለዚህ አንድ ሰው ለዘላለም እህል ሲወቃ አይኖርም። የመውቂያውን መንኰራኵር ቢያኼድበትም፣ ፈረሶቹ አይደፈጥጡትም።
ለዚሁ፣ የሙታንና የሕያዋን ጌታ ይሆን ዘንድ ክርስቶስ ሞቷል፤ በሕይወትም ተነሥቷል።