ወዮ ለዚያ ቀን! የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና፤ ከሁሉን ቻይ አምላክ እንደ ጥፋት ይመጣል።
እግዚአብሔር ግን ይሥቅባቸዋል፣ ቀናቸው እንደ ደረሰ ያውቃልና።
ወዮ ለዚያ ቀን! እንደዚያም ያለ አይኖርም፤ ለያዕቆብ የመከራ ጊዜ ነው፤ ነገር ግን ይተርፋል።
ያ ቀን ግን የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን ነው፤ ጠላቶቹን የሚበቀልበት የበቀል ቀን። ሰይፍ እስኪጠግብ ድረስ ይበላል፤ ጥማቱም እስኪረካ ድረስ ደም ይጠጣል። በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር መሥዋዕት አዘጋጅቷልና።
ቀኑ ቅርብ ነው፤ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፤ የደመና ቀን፣ ለአሕዛብም የጥፋት ቀን ነው።
በሰራዊቱ ፊት፣ እግዚአብሔር ያንጐደጕዳል፤ የሰራዊቱ ብዛት ስፍር ቍጥር የለውም፤ ትእዛዙንም የሚያደርግ እርሱ ኀያል ነው፤ የእግዚአብሔር ቀን ታላቅ፣ እጅግም የሚያስፈራ ነው፤ ማንስ ሊቋቋመው ይችላል?
ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ከመምጣቱ በፊት፣ ፀሓይ ወደ ጨለማ፤ ጨረቃም ወደ ደም ትለወጣለች።
ብዙ ሕዝብ፣ በጣም ብዙ ሕዝብ፣ ፍርድ በሚሰጥበት ሸለቆ ተሰብስቧል፤ ፍርድ በሚሰጥበት ሸለቆ፣ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና።
“በአሕዛብ ሁሉ ላይ፣ የእግዚአብሔር ቀን ደርሷል፤ አንተ እንዳደረግኸው፣ በአንተም ላይ ይደረጋል፤ ክፉ ሥራህም በራስህ ላይ ይመለሳል።
በጌታ እግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ፤ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና። እግዚአብሔር መሥዋዕት አዘጋጅቷል፤ የጠራቸውንም ቀድሷል።
ወንድሞች ሆይ፤ እርስ በርሳችሁ አታጕረምርሙ፤ አለዚያ ይፈረድባችኋል፤ እነሆ፤ ፈራጁ በበር ላይ ቆሟል።
ታላቁ የቍጣቸው ቀን መጥቷልና፤ ማንስ ሊቆም ይችላል?” አሏቸው።