ዕርሻዎች ባዷቸውን ቀርተዋል፤ ምድሩም ደርቋል፤ እህሉ ጠፍቷል፤ አዲሱ የወይን ጠጅ ዐልቋል፤ ዘይቱም ተሟጧል።
ብታርሳትም ፍሬዋን አትለግስህም፤ በምድር ላይ ኰብላይና ተንከራታች ትሆናለህ።”
የኔምሬ ውሆች ደርቀዋል፤ ሣሩ ጠውልጓል፤ ቡቃያውም ጠፍቷል፤ ለምለም ነገር አይታይም።
በየአደባባዩ የወይን ጠጅ ያለህ እያሉ ይጮኻሉ፤ ደስታው ሁሉ ወደ ሐዘን ይለወጣል፤ ሐሤቱም ሁሉ ከምድር ገጽ ጠፍቷል።
አዲሱ የወይን ጠጅ ዐለቀ፤ የወይኑም ተክል ደረቀ፤ ደስተኞችም ሁሉ አቃሰቱ።
በፊቴ ባድማ፣ ደረቅና ወና ይሆናል፤ መላዪቱም ምድር ጠፍ ትሆናለች፤ ስለ እርሷ የሚገድደው የለምና።
ምድሪቱ በዝናብ ዕጦት የምትጐዳው፣ የሜዳውም ሣር ሁሉ በድርቅ የሚመታው እስከ መቼ ነው? ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ፣ እንስሳትና አዕዋፍ ጠፍተዋል፤ ደግሞም ሕዝቡ፣ “በእኛ ላይ የሚሆነውን አያይም” ብለዋል።
ከሞዓብ የአትክልት ቦታና ዕርሻ፣ ሐሤትና ደስታ ርቋል፤ የወይን ጠጅ ከመጭመቂያው እንዳይወርድ አድርቄዋለሁ፤ በእልልታ የሚጨምቀውም አይገኝም፤ በዚያ ድምፅ ቢሰማም፣ የእልልታ ድምፅ አይደለም።
ስለዚህ ምድሪቱ አለቀሰች፤ በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ ኰሰመኑ፤ የምድር አራዊት፣ የሰማይ ወፎች፣ የባሕርም ዓሦች ዐለቁ።
የእህል ዐውድማዎችና የወይን መጭመቂያዎች ሕዝቡን አይመግቡም፤ አዲሱም የወይን ጠጅ ይጐድልባቸዋል።
ወይኑ ደርቋል፤ የበለስ ዛፉም ጠውልጓል፤ ሮማኑ፣ ተምሩና እንኮዩ፣ የዕርሻው ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፤ ስለዚህ ደስታ፣ ከሰው ልጆች ርቋል።
እናንተ ሰካራሞች፤ ተነሡ፤ አልቅሱ፤ እናንተ የወይን ጠጅ ጠጪዎች ሁሉ፤ ዋይ በሉ፤ ስለ አዲሱ የወይን ጠጅ ዋይ ብላችሁ አልቅሱ፤ አፋችሁ ላይ እንዳለ ተነጥቃችኋልና።
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል፤ “እህል፣ አዲስ የወይን ጠጅና ዘይት፣ እስክትጠግቡ ድረስ እሰጣችኋለሁ፤ የሕዝቦች መዘባበቻ አላደርጋችሁም።
ኀይላችሁ በከንቱ ያልቃል፤ ምድራችሁ እህሏን፣ የምድሪቱ ዛፎችም ፍሬዎቻቸውን አይሰጡምና።
ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያፈራ፣ ከወይን ተክልም ፍሬ ባይገኝ፣ የወይራም ዛፍ ፍሬ ባይሰጥ፣ ዕርሻዎችም ሰብል ባይሰጡ፣ የበጎች ጕረኖ እንኳ ባዶውን ቢቀር፣ ላሞችም በበረት ውስጥ ባይገኙ፣
እኔም በዕርሻዎችና በተራሮች፣ በእህሉና በአዲሱ ወይን ጠጅ፣ በዘይቱና ምድር በምታፈራው ሁሉ፣ በሰውና በእንስሳ፣ በእጆቻችሁም ሥራ ላይ ድርቅ አመጣሁ።”
“ዘራችሁን እገሥጻለሁ፤ የመሥዋዕታችሁን ፋንድያ በፊታችሁ ላይ እበትናለሁ፤ እናንተም ከርሱ ጋራ ትወገዳላችሁ፤