ግርማው እንዳያስፈራኝ፣ እግዚአብሔር በትሩን ከእኔ ላይ ቢያነሣ፣
ግርማው አያስደነግጣችሁምን? ክብሩስ አያስፈራችሁምን?
በፊቱ የደነገጥሁትም ለዚህ ነው፤ ይህን ሁሉ ሳስብ እፈራለሁ።
የእግዚአብሔርን ቍጣ በመፍራቴ፣ እንዲህ ያሉ ነገሮች መፈጸም አልቻልሁም።
እኔን መፍራት የለብህም፤ እጄም ሊከብድብህ አይገባም።
“ልቤ በዚህ በኀይል ይመታል፤ ከስፍራውም ዘለል ዘለል ይላል።
ክንድህን አንሣልኝ፤ ከእጅህ ምት የተነሣ ደክሜአለሁ።
ሰዎችን ስለ ኀጢአታቸው ለመቅጣት ትገሥጻቸዋለህ፤ ሀብታቸውንም ብል እንደ በላው ታደርጋለህ፤ በርግጥ ሰው ሁሉ ተን ብቻ ነው። ሴላ
ኀጢአታቸውን በበትር፣ በደላቸውን በጅራፍ እቀጣለሁ።
የቍጣህን ኀይል ማን ያውቃል? መዓትህም የመፈራትህን ያህል ታላቅ ነው።