ሰው ከርሱ ጋራ ለመከራከር ቢፈልግ፣ ከሺሕ ጥያቄ አንዱን እንኳ መመለስ አይችልም።
እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፤ በምን ላይ እንዳልተስማማን ንገረኝ እንጂ አትፍረድብኝ።
ሊከስሰኝ የሚችል አለ? ካለም፣ ዝም ብዬ ሞቴን እጠብቃለሁ።
የሰውን አቤቱታ እንደማይሰማ፣ ለምን ታማርርበታለህ?
ሰው ለፍርድ ፊቱ ይቀርብ ዘንድ፣ እግዚአብሔር ቀጠሮ አይዝለትም።
“ከሁሉን ቻይ አምላክ ጋራ ተከራክሮ የሚረታው አለን? እግዚአብሔርን የሚወቅሥ እርሱ መልስ ይስጥ!”
አንድ ጊዜ ተናገርሁ፤ የምመልሰው የለኝም፤ ሁለተኛም ተናገርሁ፤ ከእንግዲህ አንዳች አልጨምርም።”
“ታዲያ፣ ከርሱ ጋራ እሟገት ዘንድ፣ ልከራከረውም ቃላት እመርጥ ዘንድ፣ እንዴት እችላለሁ?
ንጹሕ ብሆን እንኳ፣ አንደበቴ ይፈርድብኛል፤ እንከን የለሽ እንኳ ብሆን፣ በደለኛ ያደርገኛል።
ስሕተቱን ማን ሊያስተውል ይችላል? ከተሰወረ በደል አንጻኝ።
ስፍር ቍጥር የሌለው ክፋት ከብቦኛልና፤ የኀጢአቴ ብዛት ስለ ያዘኝ ማየት ተስኖኛል፤ ከራሴ ጠጕር ይልቅ በዝቷል፤ ልቤም ከድቶኛል።
ነገር ግን ለእግዚአብሔር መልስ የምትሰጥ አንተ ማን ነህ? “ሥራ ሠሪውን፣ ‘ለምን እንዲህ ሠራኸኝ?’ ይለዋልን?”
ኀጢአት የለብንም ብንል፣ ራሳችንን እናስታለን፤ እውነቱም በእኛ ውስጥ የለም።
ይህም ልባችን በእኛ ላይ በሚፈርድብን ነገር ሁሉ ነው። እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉን ነገር ያውቃል።