ሁሉም አንድ ነው፤ ‘እርሱ ጻድቁንና ኀጥኡን ያጠፋል’ የምለውም ለዚህ ነው።
የክፉዎችን ዕቅድ በደስታ እየተቀበልህ፣ እኔን ግን ስታስጨንቀኝ፣ የእጅህንም ሥራ ስታዋርድ ደስ ይልሃልን?
እኔ በደለኛ እንዳልሆንሁ፣ ከእጅህም ሊያስጥለኝ ማንም እንደማይችል አንተ ታውቃለህ።
“እጅህ አበጀችኝ፤ ሠራችኝም፤ መልሰህ ደግሞ ታጠፋኛለህን?
ለሕያዋን ሁሉ ወደ ተመደበው ስፍራ፣ ወደ ሞት እንደምታወርደኝ ዐውቃለሁ።
ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት በጠፋ፣ ሰውም ወደ ዐፈር በተመለሰ ነበር።
‘እግዚአብሔርን ለማስደሰት መሞከር፣ ለሰው አንዳች አይጠቅምም’ ብሏልና።
“የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፤ “ ‘ሰይፍ! ሰይፍ! የተሳለ የተወለወለም፤