እግዚአብሔር ቍጣውን አይመልስም፤ ረዓብን የሚረዱ እንኳ ይሰግዱለታል።
በኀይሉ ባሕርን ያናውጣል፤ በጥበቡም ረዓብን ይቈራርጣል።
“ከሚያውቁኝ መካከል፣ ረዓብንና ባቢሎንን እጠቅሳለሁ፤ እነሆ፤ ፍልስጥኤምና ጢሮስ ከኢትዮጵያ ጋራ፣ ‘ይህ ሰው በዚያ ነው የተወለደው’ ይላሉ።”
አንተ ረዓብን የተሰየፈ ያህል አደቀቅኸው፤ በብርቱ ክንድህም ጠላቶችህን በተንሃቸው።
ርዳታዋም ፈጽሞ ዋጋ ቢስ ወደ ሆነው ወደ ግብጽ ይሄዳሉ። ስለዚህ ስሟን፣ ረዓብ፣ ምንም የማትጠቅም ብዬ እጠራታለሁ።
የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነድዷል፤ እጁን አንሥቶ መትቷቸዋል፤ ተራሮች ራዱ፤ ሬሳዎችም በመንገድ ላይ እንደ ተጣለ ጥራጊ ሆኑ። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።
የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ፤ ተነሥ፤ ተነሥ! ኀይልን ልበስ፤ እንዳለፉት ዘመናት፣ በጥንት ትውልዶችም እንደ ሆነው ሁሉ ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ፣ ታላቁን ዘንዶ የወጋህ አንተ አይደለህምን?