ነገር ግን አንተ ወደ እግዚአብሔር ብትመለከት፣ ሁሉን ቻይ አምላክን ብትማፀን፣
“ነገር ግን ልብህን ብትሰጠው፣ እጅህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፣
“እነሆ፤ እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ብፁዕ ነው፤ ስለዚህ ሁሉን ቻይ አምላክ ተግሣጽ አትናቅ።
“እኔ ብሆን ኖሮ፣ ወደ እግዚአብሔር በቀረብሁ፣ ጕዳዬንም በፊቱ በገለጽሁለት ነበር።
ጻድቅ ብሆንም እንኳ፣ ልመልስለት አልችልም፤ ዳኛዬን ምሕረት ከመለመን ሌላ ላደርግ የምችለው የለም።